የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ባአስቸካይ ግዜ አዋጅ ላይ የሰጠው መግለጫ ! EPPF Communique Against the State of Emergency in Ethiopia N° 2018/01 N° 2018/01

የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ባአስቸካይ ግዜ አዋጅ ላይ የሰጠው

መግለጫ N° 2018/01

የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች  ግንባር ከተመሰረተ እ ኤ አ ከ 1998 ዓ ት ጀምሮ  ላለፉት 20 ዓመታት ወያኔ በኢትዮጵያውያን ላይ እየፈጸመ ያለውን ሰቆቃ እና መከራ በመታገል ላይ ይገኛል።

 

አርበኛው  በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጭ የወያኔን ግፍና በደል ሲጋፈጥ እና ሲያጋልጥ ውሎ አድሯል።

 

አርበኛው ወያኔ የሚፈጽማቸውን ኢትዮጵያውያንን አደጋ ላይ በሚጥሉ ውንጀሎችንና መቅስፍቶችን  በመቃወም ከጥፋቱ  እንዲታቀብ  ደጋገሞ አስጠንቅቋል።

 

የወያኔ በ2016 ያወጀው ያማይገባ የአስቸኳይ ግዜ አዋጅዜጎቻችን ላይ ከፍተኛ ጉዳት አደርሷል። ይህም በሰላሳ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎቻችንን አሰረዋል የሺዎችን ሕይወት አጥፈተዋል።

 

  ኮማንድ ፖስቱን የሚያስፈጽሙ የፖሊስ እና የሚሊቴሪ አባላት የፈለጉት ቤት በማንኛውም ሰዓት በመግባት ከፍተኛ የሆነ ኢሰባዊ ድርጊቶችን መፈጸማቸው የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው በተጨማሪ ህይወታቸው ያለፈ በመኖራቸውም ዜጎች ወተው በሰላም መመለስ አስቸጋሪ እንዲሆን አድርጎት ነበር።

 

ለሁለተኛ ጊዜ እ.ኤ.አ. የካቲት 16፣ 2018 የታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ያልተገባ ከመሆኑም ባሻገር ዜጎች ላይ የሚያስከትለው ኢሰባዊ ግፎችን ከግምት በማስገባት እና ደግሞ የዜጎችን ድምጽ በማፈን የወያንኔ ስልጣን ለማራዘም የታቀደ መሆኑ ግልጽ ስለሆነ እና ይህ የማይገባ  የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሀገሪቷን ወዳልተፈለገ  አቅጣጫ ሊያመራት ስለሚችል፣                በአርበኛው  ይህን  የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በማውገዝ የተሰጠ መግለጫ፦

 

  1. በሀገሪቱ በአጠቃላይ በሚባል ደረጃ እየተካሄደ ያለውን  ተቃውሞ  በማፈን ዜጋዊ ትግሉን ለማኮላሸት የተደረገ ሴራ በመሆኑ አርበኛው ያወግዘዋል።
  2. የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር የመጀመሪያውንም ሆነ ሁለተኛውን የአስቸኳ ጊዜ አወጅ በጽኑ ይቃወማል እንዲሻርም ያሳስባል።
  3. እደሚታወቀው የአስቸኳይ ግዜ አዋጁ ዝርዝር ማስፈጸሚያ ያለገደብ ስልጣንን ለታጣቂዎች ማለትም ለፖሊስ ኅይል እና ለመከላከያ ሰራዊቱ ስለሚሰጥ ግድያ የጭካኔ ድብደባና የጅምላ እስር  ስለሚፈጸም ኢህአግ በጽኑ ይቃወማል።

 

  1.  ማስፈጸሚያ ዝርዝሩ ያለፍርድ ቤት ትእዛዝ የዜጎችን መኖሪያ ቤቶች የንግድ  ቦታዎች እና የተለያዩ አገልግሎት መስጫ የግል ተቋሞችን  መፈተሽ ስለሚያስችለው የህብረተሰቡን ንብረት እና ገንዘብ በታጣቂዎች ስለሚዘረፍ  ኢ ሕ አ ግ  አጥብቆ ይቃወማል።

 

  1.    በመጨረሻም ወያኔ ዜጋዊ እምቢተኝነቱን በአስቸኳ ግዜ አዋጅ ለማፈን ቢሞክርም፣  ተቃውሞዎች በተለያዩ የሀገሪቷ ክፍሎች እየተካሄደ ይገኛል።

ገፈኛው ወያኔ አስራአንደኛው ሰዓት  ላይ መድረሱን በመንገዘብ ከወደቁ በኋላ መፈራገጥ ለመላላጥ  እንዲሉ፣

አርበኛው   ስልጣኑን ካለ ቡዙ ደም መፋሰስ  ባስቸኳይ ላገሪቱ ዜጋዎች  እንዲያስረክብ ሲል ባአንከሮ ያስጠነቅቀዋል።

                        ድል ለሰፊው ህዝን

                       ሞት ለወያኔ

                         አንደነት ሃይል ነው !

                        ኢይዮጵያ ለዘላለም ትኑር

EPPF Communique Against the State of Emergency in Ethiopia N° 2018/01 የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ባአስቸካይ ግዜ አዋጅ ላይ የሰጠው from Ethiopianism Prof. Muse Tegegne on Vimeo.

Tagged with 

Comments are closed.