Ethiopia #EPPF Communique Against Abiy’s Regime in Ethiopia ከአርበኞች የተሰጠ መግለጫ 2019/01
——
የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር የወያኔ / ኢሃዴግ አቢይ መንግስት በታቀደና በተጠና መልኩ በመላ ሃገሪቱ በዜጎቻችን ህይወት ላይ እየተደረገ ያለውን በዘር ላይ ያነጣጠረ የዘር ማጥፋት እና መከኖሩበት ቀዬ የማፈናቀልን በጥብቅ ያወግዛል ፡፡
የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ላለፉት 21 አመታት በኢትዮጵያ ርሃብ ፣ ስደት፣ መሬት ወረራ፣ ግድያ ፣ አፈና ፣ የዜጎች ከቦታ ቦታ የመንቀሳቀስ እና በመረጡበት ቦታ ሃብት የማፍራት መብት እና ባጠቃላይ ሀያ አራቱ የወያኔ መቅሰፍትን እንዲያበቁ ይታገላል ፡፡
የኢትዮጲያ ህዝብ አርበኞች ግንባር እ.ኤ.አ ከ 1998 እስከ 2008 ድረስ በኤርትራ ውስጥ ሲታገል የቆየ ቢሆንም አሸባሪው የሻቢያ መንግስት ከወያኔ ጋር በመሆን ግንባራችን ላይ ከፍተኛ የሆነ የማደናቀፍ ስራ በመስራቱ ድርጅታችን ኤርትራን ለቆ በመውጣት ትግሉን በአጋር ሃገራት በመታገዝ በሀገር ውስጥ ለዜጎች ነጻነት በመታገል ላይ ይገኛል ፡፡
በአሁኑ ሰአት በሃገራችን ላይ በሰፊው ተንሰራፍቶ የሚጘኘውን ጽንፈኛ የሆነ የዘር ፖለቲካ ምክንያት የኢትዮጲያ ዜጎች በሰላም እንዳይኖሩ እና የሰላም አየር እንዳይተነፍሱ ከላይ በስልጣን ማማ ላይ በተቀመጡ በኢትዮጲያዊነት ካባ ተሸፍነው እውነታውን ለመሸፈን እና ሽፋን በመስጠት በውስጥ ቀጥተኛ የሆነ ኦነጋዊ ጽንፈኛ አስተሳሰብን በተግባር እየተፈጸመ ይገኛል ፡፡
፩ የዜጎች መፈናቀል እና ርሃብ
# በሃገራችን በሰላም እና በመተሳሰብ የሚኖሩ ህዝቦችን ለፖለቲካ ፍጆታ ሲባል በዘራቸው ምክንያት ብቻ ከኖሩበት እና ሃብት ካፈሩበት ስፍራ እንዲፈናቀሉ እንዲሁም ሴቶች በአደባባይ ለመደፈር ይገደዳሉ ለዚህም ማስረጃ የሚሆኑ
# በጌዲዮ ፣ በባስኬቶ ፣ በጎንደር ፣ በለገጣፎ ፣ በሰበታ ፣ እንዲሁም በቀጣይ በሱሉልታ በአጠቃላይ ባለፉት ጊዜአት እና አሁን ከ 3.2 ሚልዮን በላይ የሚሆኑ ዜጎች በሃገራቸው የተፈናቀሉ እንዲሁም ከ 8. ሚልዮን በላይ ለከፋ ርሃብ እና ስደት የተዳረጉ ዜጎች የሚኖሩባት ሃገር ሆናለች
፪ አዲሥ አበባን ጉዳይ
# በሃገራችን ኢትዮጲያ ከ 83 በላይ ቋንቋ የሚነገርባት ሃገር ዋና ከተማ የሆነችውን አዲሥ አበባን አንስቶ ለአንድ ቋንቋ ተናጋሪ ወይንም ለኦሮምኛ ተናግሪው የባለቤትነት መብትን ለመስጠት የሚደረግ እሩጫ እና በከተማዋ ለሚኖረው የዜጎችን ስብጥር (demography ) ወደ ኦሮሚኛ ለመቀየር በሚደረግ ጽንፈኝነት ምክንያት ነዋሪዎቿን እና ሃገሪቷን ስጋት ላይ መጣል ፡፡
# ዜጎች ካላቸው ከእጅ ወደአፍ ኑሮ ላይ ቆጥበው የሰሩትን የጋራ መኖርያ ህንጻዎች ባለቤት እንዳይሆኑ የሚደረገውን ሴራ
# አዲስ አበባን ወደ ኦሮሚያ ክልል ለማጠቃለል ሲባል ይህግ የበላይነትን ለማስከበር በሚል ሽፋን በዙሪያዋ ያሉ አነስተኛ ከተሞች ላይ በላባቸው የሰሩትን ቤት ዜጎች ዘራቸው እየተመረጠ እንዲፈርስ መደረግ እና የዘር ማጽዳት ዘመቻ ፡፡
፫ በሃገሪቷ ላይ እየተከሰተ ያለውን ቀውስ መረጃን መደበቅ
# ከዜጎች እና ከሃገር ይልቅ የራሳቸው ስልጣንን ለመጠበቅ ሲባል በሃገር ውስጥ ሰላም ፣ ፍትህ ፣ ዴሞክራሲ እንደሰፈነ ለማስመሰል የሚሰራ ፕሮፖጋንዳ ፡፡
# ከ8 ወራት በላይ በጌዲዮ የሚኖሩ ዜጎች በርሃብ አለንጋ ሲረግፉ ለስልጣናቸው መናጋት እንዳይፈጠር ሲባል ወገን እና ግብረሰናይ ድርጅቶች እንዳይደርሱላቸው መረጃን ሆን ብሎ ማፈን ፣
# ከ 18 በላይ የህዝብ ሃብት የሆኑ ባንኮች ተዘርፈው ዘራፊዎችን ለህግ ላለማቅረብ የሚሰሩ ስራዎች፣
# እርስ በርሱ የሚጣረስ መረጃዎችን መስጠት እና አቋም የሌለው ውሳኔዎችን ማስተላለፍ፣
# ሃገር በአራቱም አቅጣጫ በዘር ፣ በጎሳ ፣ በቋንቋ እና በማንነት ጉዳይ ተወጥራ ባለችበት ሰአት ለሚድያ ሲባል የሚሰራ ፕሮፖጋንዳ ፡፡
እነዚህን ከላይ የጠቀስናቸው ጉዳዮች ዋነኛ ተጠያቂ በስልጣን ላይ ያለው የአቢይ መንግስት ነው ፡፡ አርበኛው እንዚህን ጉዳዮች ከምንም በላይ የሚያወግዘ እና በፍጹም የማይታገሳቸው ናቸው ፡፡
ድል ለዜጎቻችን!
አንድነት ሃይል ነው !!!!!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር !!!
አርበኛው መጋቢት 2019
ከኢትዮጲያ ህዝብ አርበኞች የተሰጠ መግለጫ ፡፡