EPPF Communique November 1, 2019/03 Oromia Massacre Responsibilities!

ከኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር የተሰጠ መግለጫ ቁጥር  2019 / 03

በኦሮሞ ባንቱስታን ለደተረገው ጭፍጨፋ

ABbiyy.png

   የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር የወያኔ / ኢሃዴግ አቢይ መንግስት ስልጣን ከተቆናጠጠ ጀምሮ በታቀደና በተጠና መልኩ በተከታታይ በመላ ሃገሪቱ በዜጎቻችን ህይወት ላይ እየተደረገ ያለውን በዘር ላይ ያነጣጠረ የዘር ማጥፋት እና ከኖሩበት ቀዬ ማፈናቀልን በጥብቅ ያወግዛል ፡፡

አርበኛው ላለፉት 21 አመታት በኢትዮጵያ ርሃብ ፣ ስደት፣ መሬት ወረራ፣ ግድያ ፣ አፈና ፣ የዘር ማጽዳት ፣ የዜጎች ከቦታ ቦታ የመንቀሳቀስ እና በመረጡበት ቦታ ሃብት የማፍራት መብት እና ባጠቃላይ ሀያ አራቱ የወያኔ መቅሰፍትን እንዲያበቁ ይታገላል ፡፡
  አርበኛው በግንባር እ.ኤ.አ ከ 1998 እስከ  2008 ድረስ በኤርትራ ውስጥ ሲታገል የቆየ ቢሆንም አሸባሪው የሻቢያ መንግስት ከወያኔ ጋር በመሆን ግንባራችን ላይ ከፍተኛ የሆነ የማደናቀፍ ስራ በመስራቱ ድርጅታችን ኤርትራን ለቆ በመውጣት ትግሉን በአጋር ሃገራት በመታገዝ በሀገር ውስጥ ለዜጎች ነጻነት በመታገል ላይ ይገኛል ፡፡
     በአሁኑ ሰአት በሃገራችን ላይ በሰፊው ተንሰራፍቶ የሚጘኘውን ጽንፈኛ የሆነ የዘር ፖለቲካ ምክንያት የኢትዮጲያ ዜጎች በሰላም እንዳይኖሩ እና የሰላም አየር እንዳይተነፍሱ ከላይ በስልጣን ማማ ላይ በተቀመጡ በኢትዮጲያዊነት ካባ ተሸፍነው እውነታውን ለመሸፈን እና ሽፋን በመስጠት በውስጥ ቀጥተኛ የሆነ ኦነጋዊ ጽንፈኛ አስተሳሰብን በተግባር እየተፈጸመ ይገኛል ፡፡

፩ ለሽብርተኞች ድጋፍ መስጠት 
ከዜጎች ከእጅ ወደ አፍ ከሆነ ኑሮ ላይ በተሰበሰበ የግብር ገንዘብ ቀጥተኛ የሆነ የገንዘብ እና የቁሳቁስ ድጋፍ በማድረግ ጽንፈኞች የራሳቸውን ሚድያ በሃገር ውስጥ እንዲከፍቱ በመፍቀድ ዘረኝነትን ፣ጥላቻን ፣ጽንፈኝነት እና የዘር ማጽዳትን እንዲሁም ሃገር ለማፍረስ ሌት ተቀን ስብከት ለሚሰሩ ግለሰቦች በመንግስት የሚመራ የግል ጥበቃ በማድረግ ፡፡ በየለቱ ኢትዮጵያውያን ዜጎች ላይ በመላ ሃገሪቱ ሽብርን በመፍጠር ተረኝነትን በማቀንቀን ላይ ይገኛሉ  ፡፡
፪ የዘር ማጽዳት ዘመቻ
ከኢትዮጵያውያን ባሃልና ስብእና ውጪ በሆነ ታይቶም ተሰምቶ በማይታወቅ መልኩ መንግስታዊ ከለላ እና ሽፋን በመስጠት ዜጎች ባላሰቡት እና ባልጠበቁት ሰአት የመንጋ ፍርድን በመስጠት አንገት መቅላት ፣ የሴትን ልጅ ጡት መቁረጥ ፣ በድንጋይ እና በዱላ ድብደባ በማድረግ ከፍተኛ የሆነ የዘር ማጽዳት ሂደት በደብረዘይት ፣ በናዝሬት ፣ በአሩሲ ፣ በባሌ ፣ በሃረር ፣ በድሬደዋ ተካሂዷል ፡፡

፫  በሃይማኖት ተቋማት ላይ የሚደረግ ዘመቻ
እርስ በርስ ተከባብሮ አንዱ የአንዱን ሃይማኖት አክብሮ በጋራ ለብዙ ዘመናት አብሮ የሚኖርን ማህበረሰብን ለመከፋፈል እና ልዩነትን ለመፍጠር እና የፖለቲካ ትርፍን ለማግኘት ሲባል የሃይማኖት ተቋማትን ማቃጠል አገልጋዮችን መግደል ማዋረድ ዜጎችን ተስፋ ለማስቆረጥ የሚሰራ ቀጥተኛ የሆነ የወያኔ ኦነግን አላማን የማሳካት ሃገርን የመበተን እርምጃዎች ፡፡
፬ የመደራጀት መብት 

ዜጎች በነጻነት መብታቸውን የመጠየቅ ፣ ሃሳባቸውን የመግለጽ ፣ የመሰብሰብ እና ሰላማዊ ሰልፍን የማድረግ መብትን በመንፈግ የተረኝነት ፖለቲካ በማራመድ ለተወሰነ ቡድን ብቻ ነጻነትን በማጎናጸፍ ዜጋ እና ሁለተኝ ዜጋን መፍጠርና አፓርታይድን ማካሄድ ፡፡
፭ . የፍትህ መዘግየት
የዘገየ ፍትህ እንደቀረ ይቆጠራል ፡፡ የዶክተር አቢይ አስተዳደር ወደ ስልጣን ከመጣ ጀምሮ የተሰሩ ወንጀሎች እንዲሁም ለሀያ ስምንት አመታት በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ግፍ ፣ ግድያ ፣ አሰቃቂ እስራት ፣  ሃገር ሲሸጡና የሃገር ሃብት ሲዘርፉ የነበሩ ወንጀለኞች እንዲሁም በሰኔ 16 የቦንብ ጥቃት ፣ የኢንጅነር ስመኘው ግድያ ፣ በቡራዩ በጋሞ ተወላጆች ላይ የተቀነባበረ ዘር ማጥፋት ፣ በሃይማኖት ተቋማት ላይ የእሳት ቃጠሎ እና ግድያ ፣ በጌዲኦ እና በተለያዩ የሃገሪቷ ክፍሎች ላይ ያፈናቀሉ እና የገደሉ ፣ በሰኔ 15 የአማራ ክልል አመራሮች ግድያ እና ከርሱ ጋር በተያያዘ ጉዳዩ የማይመለከታቸው የፖለቲካና ሲቭል ዜጎች በሽብር ወንጀል ክስ እና ትእስራት ፣ የሃገሪቱን ባንኮች ዘረፋ ፣ በአንድ ግለሰብ ጥሪ በዜጎች ላይ የተደረገ ይዘር ማጽዳት የተፈጸመ ወንጀል እንዲሁም ሌሎች ያልጠቀሰናቸው ወንጀሎች ባጠቃላይ ምንም አይነት ፍትህ እና የፍትህ የበላይነት አለማካሄድ ፡፡ 
 እነዚህን ከላይ የጠቀስናቸው ጉዳዮች ዋነኛ ተጠያቂ በስልጣን ላይ ያለው በዶክተር አቢይ የሚመራው  መንግስት ነው ፡፡ አርበኛው እንዚህን ጉዳዮች ከምንም በላይ የሚያወግዘ እና በፍጹም የማይታገሳቸው እንዲሁም ከዛሬ ነገ እየባሰ የመጣውን በዜጎች ላይ የሚካሄደውን የዘር ማጽዳት እና ግድያን ለመታገል ከአርበኛው ጋር በጋራ በመሆን ዜጎች በትግሉ እንዲቀላቀሉ ጥሪውን ያቀርባል ፡፡

በጭካኔ ድርጊት ለተሰዉ  የዜጎቻችን ነፍስ ፈጣሪ እንዲያስባቸው እና ለቤተሰቦቻቸው መጽናናትን እንዲሰጣቸው እንመኛለን   
ድል ለዜጎቻችን!

አንድነት ሃይል ነው !!!!

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር  !!!

አርበኛው ጥቅምት  2019
ከኢትዮጲያ ህዝብ አርበኞች ግንባር የተሰጠ መግለጫ ፡፡

About The Author