Arbegna Fano Communique on the arrest of member Meseret Kelmework!
The Ethiopian People’s Patriotic Front
የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር
ye’ītiyop’iya ḥizibi āribenyochi ginibari
July 10th, 2020
EPPF Communique statement on the arrest of our Arbegna Fano member Meseret Kelmework! No. 2020/02
The Ethiopian People’s Patriotic Front (EPPF) was founded in the North-western part of Ethiopia, on the frontier of Eritrea in the place called ‘Awegara’ under the auspices of Ethiopian democratic forces. Recognizing the political crisis and social challenges posed by the EPRDF government, EPPF began struggling with a national vision to hand over power to the people through establishing a direct and participatory democrati government.
EPPF is an organized people’s front for the realization of a political system that promotes the national identity, including individual and group rights and treats different members of the community equally. The struggle will continue until the goal of building an inclusive political system that reaffirms national unity based on Ethiopian identity. Since its formation, we have achieved many remarkable results. However, several Arbegna-Fano members have been killed in attacks by government forces on various fronts. Today members of the patriotic front continue their struggle for the liberation of Ethiopia.
The Ethiopian People’s Patriotic Front (EPPF) has been classified unjustly as a terrorist organization by the Ethiopian government in 2006. After Prime Minister Abiy Ahmed came to power in 2018, the patriotic front refused to enter the country due to the unwillingness of the government to abandon the ideological principles set by the EPRDF regime. Some Arbegna-Fano military forces found in the Eritrean premises have been forcibly repatriated by the Eritrean government. As a result, some of our militants have been killed by the government notorious action, and many have also been arrested and tortured.
In the past two years, the government has been calling on rival parties to expand the political space and establish a democratic government. However, it has been observed that the government violates and restricts the peaceful and democratic movements of those rival parties including freedom of expression. Besides, the government has also been pressuring members of the opposition political parties to work only in the direction the government has set instead of having their political strategies and principles.
Today, we are in a tragic situation where the blood of the innocent is shed by the extremist political conspiracies. The EPRDF constitutional structure is rooted in the politics of ethnic cleansing, and hatred that is being perpetrated against our citizens. The 25-year-old Ethiopian Constitution that seems the apartheid Bantustan constitutional framework has resulted in the loss of Ethiopian national identity, widespread unrest, displaced people due to their ethnic background, and massacre of thousands of people.
Recently, following a shot dead known Oromo nationalist singer called Hachalu Hundesa, the government has arrested rival political leaders who were not explicitly related to his death due to the violence that followed. As a result of the negligence shown by the government to take correcting measures on those extremist ideologies, lately the government resort to attacking the messenger and not the message. Among those arrested by the government, especially a journalist, and human rights activist Eskinder Nega, Aster Seyoum, Sintayhu Chekol, Ing. Yilkal Getnet and Lidetu Ayalew were the major ones.
It has also been known that Arbegna Fano Meseret Kelemwork, one of the EPPF members who entered the country from Australia to visit his families is currently under arrest by the government effective from July 8, 2020, in Bahir Dar, Ethiopia. Arbegna Fano Meseret Kelemwork is one of the patriots involved in various battles, has been wounded while struggling, imprisoned in Sudan, and travelled to Australia to lead the Patriotic Front. Arbegna Fano Meseret Kelemwork (nick name, Moresh) was also institutionalizing and supporting members of the Arbegna Fano who came back from Eritrea forcibly pushed by the Eritrean government and has no one to support them. In a similar context, a few months ago a former Journalist Demes Bekele, founder and head of NIgat Radio in Washington, DC, was summoned and poisoned.
We would like to remind the people of Ethiopia, Prime Minister Abiy Ahmed when he supports the Ginbot 7 armed forces, organized by Prof. Berhanu Nega, but he had left the front line, the Ethiopian People’s Patriotic Front without help. EPPF, Arbegna Fano members fought to death with no hesitation and give their life at the front of the EPRDF government. We are proud of them as our outspoken patriots who have sacrificed their life to overthrow and destroy that horrible and racist system. We are basically saddened by the Ethiopian government for not at least recognizing our patriotic struggle, and we will work to make the Ethiopian people and the international community aware of the atrocities.
During this difficult national crisis, instead of seeking a national solution together with identified political organizations, the government of Ethiopia is engaged in demilitarizing and incarcerating of political figures in the name of rule of law which has led to a massive people’s movement, detention, and destruction of citizen’s lives and their property. While expressing our sympathy over the loss of lives, and public resources, we would like to request the government to take it seriously hunting down the criminals involving a third party. However, it seems that the structure of EPRDF is at the root of the Prosperity Party (PP) while dealing with political turmoil vis-à-vis. Also, it is a fact that no one can deny Abiy’s government is not undergoing any form of change to that of the EPRDF regime.
We, therefore, call on the government to stop arresting and harassing EPPF, Arbegna Fano members and call for the unconditional release of the Arbegna Fano members who are currently in arbitrary detention. We demand the Ethiopian government to ensure the safe release of our detained members to their peaceful life and democratic struggle, in line with the government’s call for peaceful and democratic rights for rival parties.
Unity is Power!
May Ethiopia live forever!!!
EPPF Communique statement on the arrest of Arbegna Fano member Meseret Kelmework! No. 2020/02 July 10th 2020 ከኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር (ኢህአግ) የአርበኛ ፋኖ አባሎቻችንን መታሰር አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር (ኢህአግ) በሀገራችን ኢትዮጵያ የዘውግ ሥርዓት መስፈን የሚያስከትለውን የፖለቲካ ሚዛን ማጣትና ማህበራዊ ቀውሶችን በመገንዘብ ለዜጎች ፍትሃዊና ትክክለኛና አሳታፊ ዲሞክራሲያዊ መንግስት በመመስረት ስልጣኑን ለሕዝብ ለማሰረከብ እንዲቻል የበኩሉን አስተዋፅዖ ለማበርከት ሃገራዊ ራዕይን አንግቦ እ.ኤ.አ ከ1998 ዓ.ም ጀምሮ ላለፉት 22 አመታት ዘረኛነትና ኋላ ቀረነት ሥርዓተ-መንግስትን በመቃወም እየታገለ ይገኛል፡፡ በዚህ የትግል ሂደትም አመርቂ ውጤቶችን አስመዝግቧል፡፡ ይሁንና በተለያዮ አውደ ውጊያዎች በመንግስት ሀይሎች በሚፈፀምበት የማጥቃት ዘመቻ ብዙ ታጋይ የአርበኛ-ፋኖ አባላቱ ተሰውተዋል፡፡ በአሁኑ ወቅትም የአርበኛ ፋኖ አባላት እልህ አስጨራሽ ትግሉን በሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጪም እንደቀጠለ ይገኛል። አርበኛ ፋኖ ሀገራዊ ራዕይን ኮትኩቶ በማሳደግ የዘውጌ ማንነቶችን ሚዛን ጠብቆ በማደራጀት የግለሰብ እና የቡድን መብቶችን አጣጥሞ በማስተናገድ ተጓዳኝ እና ተደራቢ ማንነት ያላቸውን የተለያዩ የማህበረሰቡ አባላት በእኩልነት ማስተናገድ የሚችል የፖለቲካ ስርዓት እዉን ለማድረግ የተነሳ ህዝባዊ ግንባር ነው። በቀጣይም የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር (ኢህአግ) ወያኔ የዘረጋውን ፀረ-ዲሞክራሲያዊና አምባገነናዊ ሥርዓት በማፈራረስ በኢትዮጵያዊ ማንነት ላይ የተመሠረተ ሀገራዊ አንድነትን የሚያረጋግጥ ሁሉን አሳታፊ የፖለቲካ ሥርዓት የመገንባት ዓላማው እውን እስከሚሆን ትግሉን አጠናክሮ ይቀጥላል። የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር (ኢህአግ) ከ2006 ዓ.ም ጀምሮ በአሸባሪነት መፈረጁ ይታወሳል፡፡ ከሁለት አመት በፊት በተደረገው የወንበር ሽግሽግም አብይ አህመድ ወደ ሥልጣን ከመጣ በኃላ መንግስት የዘረኛነት ሥርዓተ-መንግስት ለመገርሰስ ቁርጠኝነት ባለማሳየቱ በሀገር ውስጥ ገብቶ ለመታገል ፈቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል፡፡ ከአርበኛ ፋኖ አባላት መካካል በኤርትራ በረሀ የነበሩ የአርበኛ ፋኖ ታጋዮች በኤርትራ መንግስት አስገዳጅነት ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገቡ ተደርጓል፡፡ እነዚህ አባላቶቻችንም ከመንግስት በሚሰነዘር ጥቃት ጥቂት የማይባሉ ተገድለዋል ብዙዎቹም ለእስርና እንግልት ተዳርገዋል፡፡ ባሳለፍናቸው ሁለት አመታት የፖለቲካ ምህዳሩን ለማስፋት እንዲቻል መንግስት ለተፎካካሪ ፓርቲዎች ባደረገው ሀገራዊ ጥሪ ወደ ሀገር ውስጥ ገብተው እንዲታገሉ በወጣው መመሪያ መሰረት መቀመጫቸውን ከሀገር ውጪ ያደረጉ የፖለቲካ ድርጅቶች ወደ ሀገር ውስጥ ገብተው እየታገሉ ይገኛሉ፡፡ ይሁንና መንግስት በመርህ ደረጃ ያስቀመጣቸውን የሰላማዊ ፣ ዲሞክራሲያዊና ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት በተለያየ ደረጃ ሲሸራርፍና ሲገድብ ተስተውሏል፡፡ ጥሪ በተደረገላቸው የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲ አባላት ላይም አሉታዊ ተፅዕኖዎችን በማሳደር መንግስት ባስቀመጠው አቅጣጫ ላይ ብቻ እንዲጓዙም ጫና ሲያሳድርባቸው ቆይቷል፡፡ በአሁን ወቅት በሀገራችን ከተበዳይ ይልቅ በዳይ የሚጮህበት በፅንፈኞች የፖለቲካ ሴራ የንፁሃን ደም የሚፈስባት አሳዛኝ ሁነት ውስጥ እንገኛለን፡፡ ዛሬ በሀገራችን ውስጥ በዜጎቻችን ላይ እየተፈፀመ ላለው የዘር ማጥፋትና ሀገር የማፍረስ ተልዕኮ የጥላቻ ፖለቲካ ዋነኛ መሰረቱ ወያኔ የጠነሰሰውና ላለፉት 29 ዓመታት ዘርን መሰረት ባደረገው ከፋፋይ የባንቱስታን አፓርታይድ ሕገ-መንግስት ኢትዮጵያ ሀገራዊ ህልውናዋን እንድታጣ፣ ሁከትና ግርግር እንዲንሰራፋ ምክንያት ሆኗል፡፡ ሰኔ 22 ቀን 2012 ዓ.ም የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ መገደል ምክንያት ተከትሎ በተነሳ ሁከትና ግርግር መንግስት ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት የሌላቸውን እና በሰላማዊ መንገድ ሀሳባቸውን በተለያዩ ነፃ መድረኮች በመግለፅ ላይ የነበሩ የፖለቲካ አመራሮችን እና ግለሰቦችን ማሰሩ ይታወቃል፡፡ አህያውን ፈርቶ ዳውላውን እንዲሉ የጉዳዩን ጠንሳሾች እና ዋና ተዋናዮች በተገቢው መንገድ በወቅቱ እርምጃ ለመውሰድ መንግስት ባሳየው ዳተኝነት እና ቸልተኝነት የፖለቲካ አለመረጋጋት እንዲፈጠር ምክንያት ሆኗል፡፡ መንግስት በቁጥጥር ስር ካዋላቸው መካከል በተለይም ጋዜጠኛና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች አቶ እስክንድር ነጋን ፣ አቶ ስንታየሁ ቸኮል፡ ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት፣ ወ/ሮ አስቴር ስዮም ፣ አቶ ልደቱ አያሌው ይገኙበታል፡፡ እንዲሁም ከአርበኛ ፋኖ አባላት መካከል ወደ ሀገር ውስጥ የገቡትና የአርበኛ ፋኖ አባላቱን በአመራር ደረጃ ድጋፍ በመስጠት ላይ የነበሩት አርበኛ-ፋኖ መሰረት ቀለምወርቅ የትግል ሰም ሞረሽ በባህር ዳር ከተማ ሐምሌ 1 አርበኛ-ፋኖ መግለጫ «አብይ አህያውን ጥሎ ዳውላውን » Arrbegna Fano Cmmunique “Abiy covet messenger, not the message !” 2012 ዓ.ም በመንግስት ልዩ ኃይሎች መታሰራቸው ታውቋል፡፡ አርበኛ ፋኖ መሰረት ቀለምወርቅ በትግል ስማቸው/ሞረሽ/ በአርበኛ ፋኖ ትግል ውስጥ ከፍተኛ ተጋድሎ ሲያደርጉ የቆዮና በተለያዩ አውደ-ውጊያዎችም ተሳታፊ የነበሩ በወያኔ ወታደሮች በትግል ላይ ቆስለው በሱዳን ታስረው ወደ አውስትራሊያ ሀገር በመጓዝ የአርበኛ ፋኖን ትግል ሲመሩ ቆይተዋል፡፡ አርበኛ ፋኖ መሰረት ቀለምወርቅ ወደ ሀገር ውስጥ የገቡበት አስገዳጅ ምክንያትም በኤርትራ በረሀ በትግል ላይ የቆዩ አርበኛ ፋኖዎችን ለማቋቋምና እራሳቸውን እንዲችሉ ድጋፍ ለማድረግ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ የጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ መንግስት በፕ/ር ብርሃኑ ነጋ የተደራጁትን የግንቦት ሰባት አባላን ሲያቋቁም ነገር ግን የትግሉ ተዋናይ የነበሩትን የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር አባላትን ያለምንም እርዳታ ሜዳ ላይ መበተኑን የኢትዮጵያ ሕዝብ በውል እንዲያውቀው ለማስገንዘብ እንወዳለን፡፡ የአርበኛ ፋኖ አባሎቻችን የሐድግ መንግስት እንዲኮላሽ ደረታቸውን ለጦር ግንባራቸውን ለጥይት በመስጠት እስከ ሞት ተፋልመዋል፡፡ አስከፊውን የዘረኛውን ሥርዓት ለማንኮታኮትና ለመገርስስ መስዋዕትነት የከፈሉ ፊት አውራሪ የሀገር አርበኞቻችን በመሆናቸውም እንኮራባቸዋለን፡፡ እነዚህን የሀገር አርበኞች መንግስት ማቋቋም እና መደገፍ ሲገባው በተቃራኒው የትግል ጓዶቻችንን በማሳደድ ላይ የሚገኝ መሆኑ በእጅጉ ያሳዘነን መሆኑን የኢትዮጵያ ህዝብ እና አለማቀፉ ማህበረሰብ እንዲያውቀው ለማድረግ እንሰራለን፡፡ ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ ትግል በዋሺንግተን ዲሲ የንጋት ራዲዮ መስራችና ሀላፊ የነበሩት ጋዜጠኛ ደምስ በለጠ ያብይን ጥሪ አክበርው ገብትው ህይወታቸው በመርዝ እንዲያልፍ ተደርጓል፡፡ በዚህ አስቸጋሪ ሀገራዊ የፈተና ወቅት የኢትዮጵያ መንግስት ለሰላማዊ ትግል ወደ ሀገር ውስጥ የጠራቸውን የፖለቲካ ድርጅቶች የመፍትሄው አካል እንደማድረግ እና ሀገራዊ መፍትሄን በጋራ ከመሻት ይልቅ በመርህ ላይ ባልተመሰረተ የፖለቲካ ዲስኩር አምባገነናዊ መንግስት በመሆን ዜጎችን ለህልፈት ለእስርና የንብረት ውድመት ዳርጓል፡፡ በተፈጠረው የዜጎች ሞትና በወደመው የህዝብ ሀብት ማዘናችንን እየገለፅን መንግስት በየጊዜው በሚያጋጥመው የፖለቲካ መፈረካከስ ምክንያት በዘመነ ኢሕአዴግ አገዛዝ የነበረውን በሀሰት ወንጅሎ የማሰር መርህ ብልፅግና ፓርቲ እንደገፋበትና ምንም አይነት የሥርዓት ለውጥ እንደሌለ ማንም የማይክደው ሀቅ ነው፡፡ በመሆኑም መንግስት የአርበኛ-ፋኖ አባላቶቻችንን ማሰርና ማንገላታት እንዲያቆም አበክረን እየጠየቅን በአሁኑ ሰዓት ያለበቂ ምክንያት በሰላማዊ ትግል ውስጥ የሚገኙ በቁጥጥር ስር ያዋላቸውን አርበኛ ፋኖዎች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈታልን ጥሪ እናቀረባለን፡፡ በመጨረሻም መንግስት ለተፎካካሪ ፓሪቲዎች ያቀረበውን ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ በእኩል የመደመጥ መብት ጥሪ መሰረት በማድረግ በእስር ላይ የሚገኙ አባላቶቻችን ደህንነታቸው ተጠብቆ በተገቢው መንገድ ወደ ሰላማዊ ትግላቸው እንዲመለሱ መንግስት የበኩሉን እንዲወጣም እንጠይቃለን፡፡ አንድነት ሀይል ነው! ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር !!! copy to UN Human Rights, EU, African Unity Amnesty International,