EPPF Communique separation of EPPF & Ginbot N° 2008/04 በኢትዮጽያ ህዝብ አርብኞች ግንባር የተሰጠ መግለጫ ቁጥር 2008 እዝባር 4 !


ግንቦት 7ና  አርበኛው አንድንት ሴራ መግልጫ!

ሰሞኑን በሚድያዎች እየተሰራጨ ያለው ግንቦት 7 ከአርበኛው ጋር በይፋ ተለያየ ተብሎ እየተነገረ ያለው የሻቢያና የውያኔን ሴራ ለማጋለጥ የውጣ መግልጫ!

የኢትዮጵያ ህዝብ አርብኞች ግንባር ውያኔንና ሻቢይን  በመታገል፣

  1. የኢትዮጵያን ባንዲራ አንደገና ማውለበልብ፣
  2. ሰላጣን ለዜጋው ለማስረክብ፣
  3. ታሪካዊ ወደቦቻችን ለማስመልስ፣
  4. መሪት ላራሹ ለመስጥት፣
  5. ኢትዮጵያዊነትን ለመመስርት ትግል ከጀምረ እነሆ 20 ዓመታትን አስልፏል።

አርበኛው እ.ኤ.አ. 1998  እስከ 2008 በኤርትራ አንባ ገነን ስር የጦር አበጋዝ ሆኖ ቆይቷል። በነዚህ 10 ዓመታት ውስጥ ድርጅቱን የግሉ ተላላኪ በማድርግ፣

ከ8 የጎጥ ካዓላማው ውጭ ከሆኑ ድረጅቶች ጋር የግዴታ ትብብርና መውሃድ እንዲዲፈጽም ተገዷል።

ከነኝህም ያፈና ሰራዎች በጣም ጎልቶ የወጣው እ.ኤ.አ. ጁን 2015 ግንቦት 7 ከሚባል የሻቢያ ተለላኪዎች ጋር ተደረገ የተባለው የፕሮፕጋንዳና የስሙላ ውሕደት ነው። ድርጅታችንም ውዲያውኑ መግለጫ በማውጣት፣ ሻባይን፣ ግንቦት ሰባትንና አርብኞች ነን ባዮችንም አጋልጧል።

ድርጅቱን ለመበታተን እነዚህ አድር ብዮይችና የሻብያ ተላላኪዎች፣ አርበኛውን የማይወክሉ ጥቂት ግለሰቦች በብርሀኑ ነጋ አማክኝነት ግንቦት 7 ከኢትዮጽያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ጋር ተዋህዶ እየሰራ ነው በማለት ሲያጭበረብሩ ቆይቷል ።

 

ያሁኑ ይባስ በማለት፣  የአርበኛውን ዓላማና ስም ለማደናቀፍና ለማዳከም ግንቦት 7 ከወያኔ ጋር መደምሩን ካወጀ ሳይውል ሳያድር፣ በይፋ ግንቦት 7ና አርበኞች ተለያይተዋል በማለት ከውያኔ ተለላኪዎች መግለጫ ሲሰጥ እየተስተዋለ ነው።

አርበኛው ለስልጣን ወይንም የፖለቲካ ጥቅም የሚታገል ሳይሆን ስልጣንን ለኢትዮጵያውያን ዜጎች ለማስረከብ በቁርጠኝነት ለዓላማው የቆመ ድርጅት ነው ። ከማንም በፊትም የወያኔን ስርአትና ሴራን ከማጋለጥ አንስቶ በነፍጥ ትግል እየታገለ ያለ ድርጅት ነው።  

አርበኛው ለወያኔ ያልተንበረከ፣ ከማንም በፊት አልደመርም ብሎ መግለጫ ያውጣ፣ ወያኔንና ሻብያን ለማስወገድ ከማንም በላይ የሰራና፣ የኢትዮጵያ አፍራሾች እራስ ምታት በመሆኑ የሰሞኑ የሚድያ ድራማ ተሸርቦበታል፣  ትላንት በሻቢያ የተጀመረው ሴራ ዛሬም በወያኔ ቀጥሏል።

 

ትናንት አርበኛው በሻቢያ ግፍና በደል  2008 ከኤርትራ ጠቅልሎ ወጧል አርበኛውን ለመበታተን ከሻብያ ጋር ሆነው አብረው ሲሰሩ የነበሩ ጥቂት ግለሰቦች ፣ ዛሬም ሻቢያና ወያኔን አንድ የኢትዮጵያ ጠላቶች መሆናቸው በተጋለጠበት ወቅት ባርበኛው ስም ለመንገድ ተንሰተዋል።

እነዚህ ግለሰቦች የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባርን አይወክሉም። ይህ ሴራ በኢትዮጵያ ጠላቶች በውያኔ አብይና ተባባሪው ሻቢያ የታቀደ የተጠነሰሰ መሆኑን መግለፅ እንወዳለን

አርበኛው ከሻቢያም ሆነ ከወያኔ ቁጥጥር ስር ውጭ ነው።

ለስልጣንም አይታገልም

አርበኛው የነጻነት ግንባር እንጂ የፖልቲካ ፓርቲ አይደለም።

አንድነት ሃይል ነው!

ኢትያጵያ ለዘላለም ትኑር!

የኢትዮጽያ ህዝብ አርብኞች ግንባር!

መስከረም 28, 2018