ወደዴሳእስር የገባሁበት ሁኔታ Samson Solomon

Samson2

አርብ 2005 sep 30 እኔ የምሰራበት አካባቢ ያለው አዲስ ከተማ ትምህርት ቤት በተማሪና ፖሊስ መሀከል እረብሻ ነበር እለት ሰኞ oct 3 2005 ነው ከቀኑ 6᎓30 ስአት አካባቢ ይሆናል የጋራጁ በር በትንሹ ተከፍቶ ነበር ተማሪወቹ በሩጫ በሩን በርግደው ሲገቡ ወታደሮቹም ተከትለዋቸው  በፍጥነት ወደ ውስጥ ዘልቀው ይገቡና ከምሰራው መኪና ስር  አንስተው እየደበደቡኝ  ያወጡኛል ምክኒያቱን አላወኩትም ለመጠየቅም ሞከርኩን የሚሰማኝ አልነበረም ብቻ ዱላው ሲያርፍብኝ ነው የሚሰማኝ በኋላም ይዘውኝ ባሻገር የጦር ሰራዊት መኪና ቆሞ ሰው እየተጫነና ሲደበደብ ደግሞ በሚቀጥለው መንገድ ከላይ ሰው ፈንጠር ብለው ይመለከቱናል ድብደባው ስለጸናብኝ ፈጠን ፈጠን ብዬ ወደ መኪናው ለመንጠላጠል ሞከርኩኝ ከኋላዬ የነበረው ታጣቂ ወገቤ በሰደፊ ሲመታኝ የያዝኩትን ብረት ለቅቄው መሬት ስዘረጋ ከዚያም ከዚህም መተው የዱላ ውርጅብኝ አወረዱብኝ የሞት ሞትን ተነስቼ የተያዙትም እርዳታ አድርገውልኝ መኪና ላይ ለመንጠላጠል ቻልኩኝ መኪናው ውስጥ በግምት ከ 30 እንበልጣለን ከአረጋዊያን ጨምሮ የአይምሮ በሽተኛ ጎዳና ተዳዳሪ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍል ትንሽ ትልቅ ሳይለይ ተጠራቅመን አንገቱን ወደ ላይ ቀና ያደረገ ስለሚመታ ከመኪና ወለል ተጣብቀን ሰው በሰው ላይ ሆነን ጉዞ ተጀመረ መጀመሪያ የወሰዱን ከርቸሌ ነበርና ከግቢው ስንደርስ ብዙ የተዘጋጁ መኪናዎችና ታጣቂዎች ግቢውን አጨናንቀዋታል መኪናው ቆመ እንድንወርድ ታዘዘን ወረድን የጠበቀን የተለመደው ዱላ ነበር ወገቤም ተጎድቶ ነበርና ሲጨምሩልኝ ልቓቓመው አልቻልኩም መሬት ላይ እወድቃለሁ ከዚያም ምን እንደሆንኩኝ አላውቀም ብቻ መኪና ከከርቸሌ ተነስቶ መንገድ ሲጀምር ነበር የነቃሁት  መኪናው በከባድ ፍጥነት ይጋዛል አካባቢዬን ስቃኝ የሚያቃስት ሌላ የሚሰማ ድምጽ አልነበረም ሰው በደም ጎርፍ የታጠበ ይመስላል ክፊኛ የተጎዳም አለ ህይወቱን በጣር ለማቆየት የሚጣጣረውን ሳይ ምነው ባልተፈጠርኩ የሚያስብል ስሜት ተሰማኝ ወደ ጆሮ ግንዴ አካባቢ ቆስያለሁ ደሜ ረግቷል እራሴን ስቸ ስለነበር የዱላ ክምር ሲያወርድብኝ አልተሰማኝም ነበር ብቻ ስቆም ይሆናል ስሜቱን የማውቀው ብዬ አይኔን ጭፍኜ በድምጽ ብቻ መከታተል ጀመርኩኝ ከታፈስነው  መሀከል አጠገቤ የነበረው በጆሮዬ ሹክ አለኝ 6ቱ በድብደባ ህይወታቸው ስላለፈ ከርቸሌ እንደቀሩ ነገረኝ እኔም ምንም አላልኩም ዝምታን መርጫለሁ ከአድካሚው ጉዞ በኋላ ምሽት ላይ ደረስን መግቢያው በሩ በወታደር ተከቧል ከኛም ቀድሞ የገባ መኪና ነበር ከአይፋው አወረዱን ደዴሳ ማለት የጦር ማሰልጠኛ የነበረ ዙሪያው በጫካና ረዣዥም ሳር የተከበበ አራዊት እንደ አንበሳና አዞም እንደሚኖር ይነገራል የወባ ትንኝ ትልቁ ፈተና ነበር ሬሳ አውጪ መኪና ሬሳ ይዞ  ከመጣንበት መኪና ጎን ሲያልፍ ተመለከትኩኝ ሜዳው ላይ ትላልቅ መጋዘን የመሰሉ በቆርቆሮ የተመታ ልዩ ስሙ ጋንት ይሉታል አለ አንድ ጋንት  ከ100 በላይ ሰው የመያዝ አቅም አለው ጫማችንን አሶለቁን እንድንገባ አዘዙን ጥዋት ምላጭ ታድሎ ተሰጠን እርስ በራሳቸን እንድንለጫጭ ተነገረን እንደታዘዝነው አደረግን ጸሀዩዋ ሁን ተብሎ እኛን ለመቅጣት የወጣች ትመስል እንደ ብረት ምጣድ ትለበልባለች እህል ውሀ አልቀመስንም ደርቀናል እኔ ክፊኛ ስለተጎዳሁ አነክሳለሁ ግማሹ ተዛዝሎ የሚሄድም አለ የጨጛራ በሽተኛም ሆድን ጨብጦ ያነባል ብቻ ደዴሳ የምድር ሲኦል ይመስላል ቀኑ መሸ ጋንት አስገቡን እንግዲህ አስተኛኘታችን ስኒ ድርድር ይባላል እግሩን ይከፍታል ከዚያም አንዱ ይገባል ያም እግሩን ይከፍታል እያለ ይቀጥላል ጧት  ከማዶ በአቅራቢያው የነበረ ወንዝ ተጠልፎ ሚፍለቀለቅ ውሀ አለች ሄደን ውሀ ተጋትነው ጥም ለመቁረጥ ብቻ አልነበረም ሆድን ነፍቶ አፒታይት እንዲዘጋልን ነበር ከኛም በፊትም ሆነ በኋላም  የደረሱት ሊያመልጥ የሞከረው ግማሹ አውሬ በላው ሬሳው ተገኘ የሚል ወሬ እንሰማለን  በዚህ ሁኔታ ሰቆቃና እርዛት ይሆናል  ከመሀላችን አንዱ የሚፈሰው ደም ባለማቆሙና ወባው ተነስታበት ሲሰቃይ ያየ ከተቀመጠበት ይነሳና ለጠባቂዎች እኔ ዶክተር ነኝ አይናችን እያየ ከሚሞት ልረዳው እድል ስጡኝ ሲላቸው በእኛ ላይ ተረማምደው የሰው ልጅ እንዲህ እንደ አህያ ሲመታ አላየሁም ዱላው የዶ /ር አናት ላይ ነበር ያረፈው መሬት እንደ ወደቀ ባህር ዛፍ ተዘረረ በወባ የሚሰቃየውን እየጎተቱት ጫፍ ቤቱ በር ላይ አነጠፊት ሰዐትም አልቆየ ሲያቃስት የነበረው ህይወቱ በዛው በበሩ ትወጣለች እኛም አዝነን ደግሞ የማን ተራ ይሆን እያልን መጠባበቅ ጀመርን አንዱ የቤት ልጅ ይመስላል ቀይ ነው ተነስቶ እየጫኌ እነዚህ ውሸታሞች ናቸው የያዙት የፕላስቲክ ጥይት ነውና እናምልጥ ይላል እንግዲህ ቤቱ ሰፊ ነው አካባቢው የነበሩት ተው ቁጭበል ይሉታል ልጁም ጩህቱን ለቀቀው የብሶቱን ያክል ጮኌ ከአራቱ አቅጣጫ አንድ ጊዜይመስል አስደገፈው ደሙ አሁንም አሁንም ማለቂያ የለውም ትንሽ ጣር አሰማ አይኑን ሰቅሎ አረፈ። መሽቶ የማይነጋ የለም ነጋ ቀይ መስቀል እስረኛውን ለማየት ይመጣል የሚባል ወሬ ሰማን ከሁለት ቀን በኋላ እህል ያልቀመሰው አንጀታችን ተስፋ ቃጠረ ምግብ የጫነች መኪና ገባና ሸራው ተፈቶ አንድ የካድሬው አዛዥ ይመስላል ዳቦ እንደ ድንጋይ እየወረወረ በእስረኛው ይሳሳቁብን ነበር አንድ ዳቦ ለማግኘት 20 በዚህ ይጋደላል ያገኘውም አልዋጥ ብሎት ዳቦውን በውሀ አርሶ በላ ወደ ማታ ኮቾሮ ታደለን ያንንም ቀስ እያልን በውሀ አበስብሰን ቆረጠምናት በሚቀጥለው ቀን  መርማሪዎች ይመጣሉ ተብሎ ነበር ሳይመጡ ቀሩ ከመሀላችን በርካታ እስረኞች ተሰወሩ ስንቆጠር ጎደልን እንግዲህ አሰሳ በፓትሎ ተጀመረ ማሳ ማሳውን ጫካ ጫካውን በመትረየስ ሊያድኑ ሄዱ ወደ ማምሻው ከጠፊት ውስጥ 5 ሰዎች ተያዙ በሀይለኛው ተደብደበዋል እግራቸው ቆስሏል ሰው ብርቱ ነው ግማሹም በአውሬ መበላታቸውን የሚያሳይ የተበጫጨቀ ጨርቅ ይዘው መጡ እነርሱንም የተ እንዳደረሱዋቸው አላወቅንም  መርማሪዎች አንድ በአንድ ቃል መውሰድ ጀመሩ ስራ ያለው ስራውን ተናገረ በመጨረሻ እንደ ጉዳያችን እየታየ  እንደሚለቁን ተናግረው ሄዱ  በቀን አንዴ የሚወረወረውን ኮቾሮ እየቀመስን ተቀመጥን  እኩለ ቀን ላይ የተወስነ ሰው ሲቀር ሌላው ወደ አዲስ አበባ ሄዱ እኛም የቀረነው በተለያየ ጊዜ መርማሪ እየመጣ እየጠየቁን ነበር ነገር ግን በየቀኑ የወታደሮቹ የካራቴ መለማመጃ ሆንን በፈለጉት ጊዜ እየጠሩ ይደበድቡናል  ከዝያም 1 ወር 22 ቀን እንደቆየሁ በዋስ እና በካባድ ማስጠንቀቅያ ተፈታሁ ።

About The Author